ዓብይ አህመድ ከፔንስ ጋር ተነጋገሩ (ቪኦኤ ዜና)

ቪኦኤ ዜና

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድን ዛሬ ማነጋገራቸውን ከዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት የምክትል ፕሬዚዳንቱ ቢሮ የወጣ መግለጫ አስታወቀ።

ዋሺንግተን ዲሲ — የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድን ዛሬ ማነጋገራቸውን ከዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት የምክትል ፕሬዚዳንቱ ቢሮ የወጣ መግለጫ አስታወቀ።
ዩናይትድ ስቴትስ ከአትዮጵያ ህዝብ ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ አጋርነት ምክትል ፕሬዚዳንቱ። በድጋሚ አረጋግጠው የሰብአዊ መብቶች አያያዝን፣ የንግዱን አካሄድ ማሻሻልና ከኤርትራ ጋር ሰላም መፍጠርን ጨምሮ “ታሪካዊ” ሲሉ የጠሩትን የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይን የለውጥ ጥረት አድንቀዋል።

Share: